ሐምሌ 14/2013 (ዋልታ) – የታንዛኒያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ባህር ዳር የደረሰ የመጨረሻው የልዑክ ቡድን ሆኗል።
ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ ማለዳ ባህር ዳር በመግባት በተፈሪ መኮንን ሆቴል ያረፈ ሲሆን፣ የኮቪድ-19 ምርመራም አድርጓል።
በምድብ ሀ የሚገኘው ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር 10 ሰዓት ላይ ጨዋታውን እንደሚያደርግ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡