የአዳጊዎች ውድድር የአትሌቲክስ ፍፃሜውን አገኘ

የካቲት 11/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ያዘጋጀው የፔፕሲ የአዳጊዎች የአትሌቲክስ ውድድር ፍፃሜውን አገኘ።

ከየካቲት 9 እስከ 11 ሲካሄድ የሰነበተው ከ17 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ውድድር ተጠናቋል።

የ800 ሜትር፣ የ2000 ሜትር መሰናክል እና 3000 ሜትር ፍፃሜ ውድድሮች የተካሄዱ ሲሆን ለአሸናፊ አትሌቶች ሽልማት ተሰጥቷል።

በ800 ሜትር ሴቶች አዳኑ ፈይሳ፣ ኤደን ከተማ እና ብርቱካን ወርቅነህ ከ1 እስከ 3 ሲወጡ፤ በወንዶች 800 ሜትር ደግሞ ቅዱስ አፅብሃ፣ ታሪኩ በቀለ እና ሮቦት ታደሰ አሸንፈዋል።

በ3000 ሜትር ሴቶች ፈያ ሐሰን ቀዳሚ ስትሆን አጂር ኩሜሳ እና ወይንሸት አቤቤ ተከትለዋት ገብተዋል። አሸናዎች የሜዳልያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ውድድሩ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ስፖርትን በማነቃቃት አዳጊ እና ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት ትልቅ አበርክቶ ይኖረዋል የሚል ተስፋ ተሰንቆበት ሲደረግ መስንበቱ ተገለጿል።

በሚኪያስ ምትኩ