የኢትዮጵያ የቮሊቦል ክለቦች በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና ለመሳተፍ ወደ ቱኒዚያ አቀኑ

የኢትዮጵያ የቮሊቦል ክለቦች

ሚያዝያ 12/2013 (ዋልታ) – ብሄራዊ አልኮል እና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በቮሊቦል የአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና ለመሳተፍ ወደ ቱኒዚያ ማቅናታቸው ተገለጸ፡፡

ብሄራዊ አልኮል እና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የክለቦች ሻምፒዮና ሲሳተፉ በሴቶች ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የ2021 የአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና ውድድርን የአፍሪካ ቮሊቦል ኮንፌዴሬሽን ማዘጋጀቱም ተገልጿል፡፡

በወንዶች ቀደም ብሎ የተጀመረ ሲሆን፣ ወላይታ ዲቻ እየተሳተፈ እንደሚገኝ ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡