የዑጋንዳ ከፍተኛ ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኘ

ነሐሴ 16/2014 (ዋልታ) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የሚገኘው የዑጋንዳ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎብኝቷል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ ለልዑካን ቡድኑ አቀባበል አድገውላቸዋል፡፡

ልዑካኑ የአስተዳደሩን የሳይበር ታለንት ልማት ማዕከል፣ የዲጂታል ኤግዚቢሽን ማዕከል እና ሌሎች የሥራ እንቅስቃሴዎች ተመልክተዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ በሚኖረው ቆይታ ኢትዮጵያ እና ዑጋንዳ በምሥራቅ አፍሪካ ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ እንዲሁም ሽብርተኝነትን ለመከላከል የሚያደርጓቸውን የትብብር ሥራዎች ለማጠናከር የሚያግዝ ውይይት እንደሚያደርጉ ከአስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የልዑካን ቡድኑ የዑጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ኦኬሎ ኦሪየም እንዲሁም የሀገሪቱ የምድር ኃይል ዋና አዛዥና የፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የልዩ ዘመቻ ከፍተኛ አማካሪ ሌተናል ጀነራል ሙሆዚ ኪኑሩጋባን ጨምሮ ሌሎች የደኅንነትና ወታደራዊ ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተ ነው፡፡