ጆሴ ሞሪንሆ ፌነርባቼን ለሁለት ዓመታት ለማሰልጠን ተስማሙ


ግንቦት 23/2016 (አዲስ ዋልታ) ፖርቹጋላዊው ጆሴ ሞሪንሆ የቱርክዬን ፌነርባቼ እግር ኳስ ቡድን ለማሰልጠን ተስማሙ።

ሞሪንሆ ሁለት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ፣ ሶስት የፕሪሚዬር ሊግ፣ ሁለት የጣሊያን ሴሪ ኤ፣ አንድ ላሊጋ እንዲሁም አንድ የዩሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ዋንጫዎች ጨምሮ በርካታ ክብሮችን አንስተዋል።

በውጤታማነታቸው የሚታወቁት የ61 ዓመቱ ፖርቹጋላዊ የቱርክዬ ፌነርባቼን ለሁለት ዓመታት ለማሰልጠን እንደተስማሙ ሰካይ ስፖርት ዘግቧል።

ጆሴ ሞሪንሆ በዋና አሰልጣኝነት 11 የእግር ኳስ ቡድኖችን ያሰለጠኑ ሲሆን ቤኔፊካን፣ ፖርቶን፣ ቸልሲን፣ ኢንተርን፣ ርያል ማድሪድን፣ ማንችስተር ዩናትድን፣ ቶተንሃምንና ሮማን ይገኙበታል።

ልዩ ሰው ነኝ (The Special one) እያሉ ራሳቸውን የሚጠሩት አወዛጋቢው ጆሴ በፈረነረጆቹ ጥር 2024 ነበር ለሁለት ዓመት ተኩል ከቆዩበት የሮማ አሰልጣኝነታቸው ተሰናብተው ያለ ስራ የቆዩት።