ለኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ በአምላክ ተሰማ አቀባበል ተደረገለት

የካቲት 7/2014 (ዋልታ) በ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ በዳኝነት ተሳትፎ አድርጎ ኢትዮጵያዊያንን ያኮራ አቋም ላሳየው ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ በአምላክ ተሰማ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አቀባበል ተደርጎለታል።

በአቀባበል መርሃ ግብሩ ላይ የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት አበበ ገላጋይ፣ የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ልዑልሰገድ በጋሻው እንዲሁም ሌሎች የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች እና የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል።

በመርሃ ግብሩ ለኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ በዓምላክ ተሰማ በፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት አበበ ገላጋይ አማካኝነት የማስታወሻ ስጦታ እንደተበረከተለት ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።