ሕገ ወጥ የሥራ ማቆም አድማ – ሕግ ይዳኘኝ

የሥራ ማቆም እርምጃ ሠራተኞች ለአንድ የተወሰነ ወቅት የሚሠሩትን ሥራ እንዲቋረጥ በማድረግ ለጋራ ፍላጎታቸው በአንድነት በመሆን አቋማቸውን የሚገልጹበት መንገድ ነው፡፡

ከሥራቸው ጋር በቀጥታ በሚገናኙ ጉዳዮች ላይ ጥያቄያቸውን ሕጉን ተከትለው ለሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላት የሚያቀርቡበትና ድምፃቸውን ለማሰማት የሚችሉበት ሕጋዊ ሥልት ነው፡፡

ሕጋዊ ባልሆነ መልኩ በመደበኛው ሁኔታ ሥራው ቢከናወን ሊገኝ የሚችለው ውጤት እንዳይኖር ማድረግ ግን ቅጣት ያስከትላል፡፡

በወንጀል ሕግ በአንቀፅ 421 መሠረት ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ሕግን ወይም ሙያውን በሚቃረን ሁኔታ በፈቃዱ የሥራ ማቆም አድማ ያደረገ እንደሆነ ወይም የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ሌሎችን የገፋፋ እንደሆነ እስከ ስድስት ወር በሚቆይ እስራት ይቀጣል፡፡

የሥራ ግዴታ ተግባሩን በአግባቡ ሳይፈጽም በመቅረቱ በመንግስት፣ በሕብረተሰቡ ወይም በግለሰብ ጥቅም ላይ ከባድ ጉዳት ደርሶ እንደሆነ እስራቱ እና መቀጮው በሕግ እስከተወሰነው ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡

ጉዳዩ በአሠሪ እና ሠራተኛ አዋጅ እንዲሁም በሀገራችን በርካታ ሕጎች ጭምር የሚታይ ነው፡፡

በብርሃኑ አበራ