ማንችስተር ዩናይትድ የእንግሊዝ ኤፍኤ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ


ግንቦት 17/2016 (አዲስ ዋልታ) ዛሬ በተካሄደው የ2023/24 የእንግሊዝ ኤፍኤ ዋንጫ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ የከተማ ተቀናቃኙን ማንችስተር ሲቲን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፎ ሻምፒዮን ሆኗል።

ማንችስተር የናይትድ በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ ባገባቸው ሁለት ጎሎች ያሸነፈ ሲሆን አሌሃንድሮ ጋርናቾ በ30ኛውና ኮቢ ማይኑ በ39 ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡ ለማንችስተር ሲቲ ዠርሚ ዶኩ በ87ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል።

የዛሬውን ድል ተከትሎ ማንችስተር ዩናይትድ 13ኛ የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫውን ማንሳት ችሏል።

ከጨዋታው ቀደም ብሎ ብዙዎች ማንችስተር ሲቲዎች እንደሚያሸንፉ ገምተው የነበረ ቢሆንም የኤሪክ ቴንሃግ ቡድን ባልተጠበቀ ሁኔታ አሸንፎ የውድድር ዘመኑን በዋንጫ መደምደም አስችሎታል።

ዋንጫውን ማሸነፉን ተከትሎ ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣዩ ዓመት ለዩሮፓ ሊግ መጫወት ይችላል።