ምክር ቤቱ የአንድ  የምክር ቤት አባልን ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ወሰነ

ጥቅምት 4/2015 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የአንድን የምክር ቤት አባል  ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ወሰኗል።

ያለመከሰስ መብቱ የተነሳው የፌደራል የፍትህ ሚኒስቴር የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የመሬት አስተዳደር ፅሕፈት ቤት ሃላፊ የነበሩትንና የከተማው ምክር ቤት አባል የሆኑት ሀቢባ ዑመርን ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ነው፡፡

ፍትህ ሚኒስቴር ባቀረበው ጥያቄ  መሠረት ግለሰቧ በክፍለከተማው በአርሶ አደርና አርሶ አደር ልጅ ሰበብ በተፈፀመ የመሬት ምዝበራ ተጠርጥረው መሆኑን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።