በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን የሚወክለው የልዑካን ቡድን አባላት አሸናኘት ተደረገለት

ቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ

ሐምሌ 07/2013 (ዋልታ) – የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን በአትሌቲክስ፣ በውሃ ዋና፣ በቴኳንዶና በብስክሌት የስፖርት አይነቶች ለሚወክሉ የልዑካን ቡድን አባላት ደማቅ የሆነ የሽኝት መርኃግብር ትላንት ምሽት ተደርጓል፡፡

በታላቁ ቤተመንግስት በተካሄደው መርኃግብሩ ለቡድኑ መልካም እድል እንዲገጥመው በመመኘት የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከቡድኑ ለተወከሉት አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ እና አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ አስረክበዋል፡፡

በሽኝት መርኃግብሩ ላይ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር እና የተለያዩ የስፖርት ዘርፍ አመራሮች መገኘታቸው ከኢትዮጵያ አትሌትክስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡