በዛምቢያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዜጎች ድምጽ በመስጠት ላይ ናቸው

ነሃሴ 6/2013(ዋልታ) – በዛምቢያ ዛሬ ጠዋት የጀመረው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዜጎች በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ረዣዥም ሰልፎች ተሰልፈው ድምጽ መስጠት ጀምረዋል፡፡
ከተቃዋሚው መሪ ሃካይንዴ ሂቺሌማ ከባድ ፈተና የገጠማቸው ፕሬዝዳንት ኤድጋር ሉንጉ በዋና ከተማዋ ሉሳካ ባለው የምርጫ ጣቢያ ላይ ድምፅ ሰጥተዋል፡፡
በምርጫ ጣቢያው ሌሎች 14 ፕሬዚዳንታዊ ዕጩዎች እንደሚወዳደሩ ቢቢሲ ዘግቧል።
ፕሬዝዳንት ሉንጉ ድምጽ ከሰጡ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “እኛ እያሸነፍን ነው የማናሸንፍ ቢሆን ኖሮ በውድድሩ ውስጥ ባልገባሁ ነበር” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ኤድጋር ሉንጉ ድምጽ ከሰጡ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች መካከል እንደነበሩ ጠቅሰው ህዝቡ ረጃጅም ሰልፎች ተሰልፎ በመምረጥ ላይ መሆኑ መመልከታቸው ገልፀዋል፡፡
የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን የምርጫውን ውጤት በ 72 ሰዓታት ውስጥ ይፋ እንደሚደረግ በዘገባው ተመላክቷል።
ምርጫው ወጣቱ ብዙ የሥራ ዕድሎችን ጨምሮ የተሻለ ተስፋን የሚያገኝበት እንደሚሆን መረጃው አስታውሷል።