በፕሪምየር ሊጉ ወልቂጤ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 1 አሸነፈ

በ10ኛ ሳምንት የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ወልቂጤ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 1 አሸነፈ፡፡

ለወልቂጤ ከተማ አብዱል ከሪም ወርቁ፣ አቡበከር ሳኒ እና አሜ መሃመድ ግቦችን ያስመዘገቡ ሲሆን ለድሬዳዋ ከተማ የጨዋታ ብቸኛ ግብ ሙኸዲን ሙሳ ማስቆጠር ችሏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ወልቂጤ ከተማ ነጥቡን 15 በማድረስ ወደ 5ኛ ደረጃ ከፍ ብሏል፡፡

(በመሰረት ተስፋዬ)