መስከረም 27/2017 (አዲስ ዋልታ) እየተካሄደ ባለው 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሰይመዋል።
የፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የሥራ ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት በምክር ቤቶቹ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ የፈጸሙ ሲሆን ከቀድሞዋ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ህገመንግስቱን ተረክበዋል።
አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በምከር ቤቱ በአምስት ድምጽ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ ነው ፕሬዚዳንት ሆነው የተሰየሙት።