አምባሳደር ዮናስ ዮሴፍ ከታንዛኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

መስከረም 23/2014 (ዋልታ) በታንዛኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዮናስ ዮሴፍ ከታንዛኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ሊበርታ ሙላሙላ ጋር ውይይት አድርገዋል ።

አምባሳደር ዮናስ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታበተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥተዋል።

የሁለቱ ሀገራትን ግንኙነት ለማጠናከር በተለያየ ጊዜ የተፈራረሙትን ስምምነቶች ወደ ትግበራ ምዕራፍ ማሸጋገር እንደሚያስፈልግ፣ ሁለቱ ሀገራት እምቅ የቱሪዝም አቅማቸውን ተጠቅመው የጋራ ተጠቃሚ ለመሆን እንዲሁም በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍም በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።

ሚኒስትር አምባሳደር ሊበርታ በበኩላቸው÷ ታንዛኒያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ከፍተኛ ፍላጎት ያላት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን መድረኮች በትብብር የመስራት ልምዳቸውን ይበልጥ በማጠናከር ለጋራ ተጠቃሚነት እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።