አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ብሔራዊ ቡድኑን ለማጠናከር 2 ተጫዋቾችን ጠሩ

መጋቢት 12/2013 (ዋልታ) – አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ብሔራዊ ቡድኑን ለማጠናከር ሁለት የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቾችን ጠሩ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን  በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከማዳጋስካር አቻው ጋር  የፊታችን ረቡዕ ጨዋታውን ደርጋል፡፡

ጨዋታው ከቀኑ 10 ሰዓት በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሚካሄድ ሲሆን፣ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ቡድኑን ለማጠናከር ሁለት ተጨማሪ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቾችን አካተዋል።

በዚህም የኢትዮጵያ ቡናው ወንድሜነህ ደረጀ እና የሰበታ ከተማው መሳይ ጳውሎስ ቡድኑን እንዲቀላቀሉ ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች መሆናቸውን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።