አቶ ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካይ ጋር ተወያዩ

ሐምሌ 10/2013 (ዋልታ) – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካይ አቱዋል ካሬ ጋር በትላንትናው ዕለት መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በውይይቱም በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ያበረከተውን አዎንታዊ ሚና አቶ ደመቀ ማብራራታቸው ተገልጿል።

በሌላ በኩል በአቢዬ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ምንም እንኳ በርካታ ተግዳሮቶች ቢገጥሙትም የአቢዬን ሰላም እና መረጋጋት በማስፈኑ ረገድ ገንቢ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝም መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካዩ ሚስተር አቱዋል ካሬ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል በተመድ የሰላም ማስከበር ተልእኮ ውስጥ እየተጫወተ ላለው ሚና ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድም በአስቸጋሪው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት የላቀ ሚና መጫወቱን በመጥቀስ አወድሰዋል።