አዋሽ ባንክና አዋሽ ኢንሹራንስ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር አካሄዱ

ሐምሌ 26/2014 (ዋልታ) “የአዋሾቹ አረንጓዴ አሻራ” በሚል መሪ ቃል አዋሽ ባንክና አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር አካሂደዋል።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ከ20 ሺሕ በላይ ችግኝ ተተክሏል።

አዋሽ ባንክ እና አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ ማኅበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት ረገድ የራሳቸውን አስተዋፅኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ ተነግሯል።

በዙፋን አምባቸው