አየር መንገዱ ወደ ላሊበላ ከተማ በረራ ሊጀምር ነው

ታኅሣሥ 21/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ ከተማ እለታዊ የበረራ አገልግሎትን ከታኅሣሥ 25 እንደሚጀምር አስታወቀ።
በኢትዮጵያ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት (ገና) በዓል የዛሬ ሳምንት በድምቀት ከሚከበርባቸው ቅዱስ ስፍራዎች መካከል ላሊበላ ቀዳሚውን ስፍራ ትይዛለች።
አሸባሪው ትሕነግ በእብሪት በከፈተው ጦርነትና ወረራ ከገባባቸው መካከል በሆነችው የቱሪዝም መዳረሻዋ ላሊበላ የአውሮፕላን በረራ መቋረጡ ይታወቃል።
የሽብር ቡድኑ የታሪካዊቷን ከተማ አውሮፕላን ማረፊያ (ላሊበላ ኤርፖርት) አውድሞ መሄዱም አይዘነጋም።