አዲስ ተሿሚዎች የሰጣቸውን ኃላፊነት በቁርጠኝነትና ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ

ጥቅምት 6/2014 (ዋልታ) በጋምቤላ ክልል አዲስ የተሾሙ የሥራ ኃላፊዎች ሕዝብና መንግሥት የሰጣቸውን ከፍተኛ ኃላፊነት በቁርጠኝነትና በታታሪነት ሊወጡ እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተደድር ኡሞድ ኡጁሉ አሳሰቡ።
አዲስ የተሾሙ የሥራ ኃላፊዎች በጋምቤላ ከተማ ውይይት አካሂደዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በመድረኩ ኃላፊዎቹ የሚሰጡት አመራር የሕዝብን ጥቅምና ደኅንነት ያስቀደመ መሆን እንዳለበት ነው ያሳሰቡት።
የብልፅግና ፖርቲ የሚያስቀምጣቸውን አቅጣጫዎችና መመሪያዎች ወደ መሬት እንዲወርድ ተገቢውን አመራር በመስጠት ረገድም ሚናቸው ከፍተኛ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አዲስ ተሿሚዎች በተመደቡበት ኃላፊነት መንግሥትና ሕዝብ የሰጣቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ቃል መግባታቸውን ከጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።