ኤሪክ ቴን ሀግ የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሆነ

ኤሪክ ቴን ሀግ

ሚያዝያ 13/2014 (ዋልታ) ማንችስተር ዩናይትድ ኤሪክ ቴን ሀግን ቀጣዩ አሰልጣኝ አድርጎ መቅጠሩን ይፋ አደረገ፡፡

በውድድር ዓመቱ ሶልሻየርን ካሰናበቱ በኋላ በጀርመናዊው ጊዜያዊ አሰልጣኝ ራልፍ ራኚክ ሲመራ የቆየው ዩናይትድ በቋሚነት ቡድኑን የሚረከበውን አዲሱ አሰልጣኝ ይፋ አድርጓል፡፡

ክለቡ የሆላንድ አያክስ አምስተርዳምን በዋና አሰልጣኝነት ሲመሩ የነበሩትን እንዲሁም ታዳጊዎችን ወደ ዋናው ቡድን በማሳደግ ለስኬት በማብቃት የሚታወቁትን ኤሪክ ቴን ሀግን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ የቀጠረው፡፡

ቴን ሀግ ቡድኑን ለሦስት ዓመት በሚቆይ ውል የተረከቡ ሲሆን ክለቡ አሁን ከገባበት የውጤት ቀውስ ማላቀቅ እና ወደ ቀደመ ዝናው መመለስ ዋነኛ ተግባራቸው መሆኑ ተዘግቧል፡፡

ኤሪክ ቴን ሃግ ኮንትራቱን ከፈረመ በኋላ “የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሆኜ መሾሜ ለኔ ትልቅ ክብር ነው፣ በጣም ተደስቻለሁ፤ የዚህን ታላቅ ክለብ ታሪክ እና የደጋፊዎችን ስሜት አውቀዋለሁ እናም የሚገባቸውን ስኬት የሚያጎናጽፍ ቡድን ለመስራት ቆርጬ ተነስቻለው” ብሏል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW