ኬንያ ደቡብ ሱዳንን 2 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋገጠች

ኬንያ ደቡብ ሱዳን

ሐምሌ 14/2013 (ዋልታ) – ኬንያ ደቡብ ሱዳንን 2 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋገጠች።

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በባህርዳር ስታዲየም እየተካሄደ በሚገኘው የመካከለኛውና የምስራቅ አፍሪካ ከ23 ዓመት በታች የእግር ኳስ ውድድር ኬንያ ደቡብ ሱዳንን 2 ለ 0 በማሸነፍ በአጠቃላይ 6 ነጥብ በመያዝ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን እንዳረጋገጠች ከኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።