ነሃሴ15/2013(ዋልታ) – የህወሓቱ ሌተናል ኮሎኔል ገብረህይወት ገብረአላፍ ከጋሳይ ግንባር በደረሰበት ከባድ ኪሳራ ለመከላከያ ሰራዊት እጁን ሰጠ።
ሌተናል ኮሎኔል ገብረህይወት በተያዘበት ወቅት 4 የተለያዩ መታወቂያዎችን ጨምሮ በሃሺሽ የተለወሱ ብስኩቶችን ይዞ መገኘቱን ከአማራ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘው መረጃ ያመላክታል።
ከዚህ ባለፈም በርከታ የባንክ አካውንቶችን ይዞ የተገኘ ሲሆን፥ ኮሎኔሉ የሚመራው ጦር እንደተበተነና ተስፋ በመቁረጥ ስርዓት የማፍረስ ተልዕኮ መያዙንም ተናግሯል።
ኮሎኔሉ በጀግናው መከላከያ ሰራዊት፣ በአማራ ልዩ ሀይል፣ የአካባቢው ሚሊሻና በህዝቡ ትብብር ከባድ ኪሳራ አጋጥሟቸዋል።
ህብረተሰቡን በየስፍራው የሚገኘውን የሽብር ቡድኑን በማጋለጥ፥ አባላት ከመከላከያ ሰራዊት፣ ከልዩ ሃይሉና ሚሊሻው ጋር በመሆን አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅም ጥሪ ቀርቧል።