ግንቦት 17/2013 (ዋልታ) – ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢኮኖሚ ነጻነት ጉዳይ ነው ሲሉ ዶክተር አረጋዊ በርሄ ገለጹ፡፡
የመገናኛ ብዙሃን ሚና ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በሚል ምክክር እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የተገኙት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሉአላዊነት፣ የእድገት አና የፍትሃዊነት ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ ነጻነት ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያውያን በመተባበር አና በአንድነት ያለማንም ድጋፍ በራሳችን ገንዘብና አውቅት መገንባት የቻልነው በአፍሪካ ትልቁ ግድብ የኢኮኖሚ ነጻነታችን ማረጋገጫ አና ማስረጃ ነው ብለዋል።
በዚህም የመገናኛ ብዙሃን ይህን አውነት ለአለም በማስተጋባት የኢትዮጵያን እድገትና ሰላም ለማረጋገጥ ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
የሃሳብ ነጻነት ለሰላም፣ ለእድገት እና ለእርካታ ቁልፍ ጥያቄ ነው ያሉት ዶክተር አረጋዊ፣ ሚዲያዎች ለሚመሩበት መርህ በመገዛት ህዝብ የሚፈልገውን መረጃ በመስጠት መንቀሳቀስ ይገባል ብለዋል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ተወካይ አቶ አበራ ወንድስን በበኩላቸው፣ ሚዲያዎች በጋራ በቁርጠኝነት መንፈስ ለሀገር መቆም የሚገባቸው ሰዓት በመሆኑ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን በተግባር ማሳየት ይኖርባችዋል ብለዋል።
በምክክር መድረኩ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
(በትዝታ መንግስቱ)