የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ውድድር የፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ይደረጋል

ጥቅምት 5/2015 (ዋልታ) ሶማሊያና ደቡብ ሱዳን የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማህበራት ምክር ቤት (ሴካፋ) የ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ውድድር የፍጻሜ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ።

ከመስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት አበበ ቢቂላ ስታዲየም ሲካሄድ የቆየው ውድድር ዛሬ ፍፃሜውን ያገኛል።

ሶማሊያና ደቡብ ሱዳን ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ዋንጫውን ለማንሳት ይፋለማሉ።

በግማሽ ፍጻሜው ሶማሊያ ዩጋንዳን እንዲሁም ደቡብ ሱዳን ታንዛኒያን በማሸነፍ ለፍጻሜው ጨዋታ ማለፋቸው ይታወሳል።

ከፍጻሜው ጨዋታ ቀደም ብሎ ከቀኑ 6 ሰዓት ዩጋንዳና ታንዛኒያ የደረጃ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ሶማሊያና ደቡብ ሱዳን የሴካፋ ዞንን ወክለው በመጋቢት ወር 2015 ዓ.ም በአልጄሪያ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ውድድር ይሳተፋሉ።

በሴካፋ ውድድር 10 አገራት ይሳተፋሉ ተብሎ ቢጠበቅም ሩዋንዳ፣ ኤርትራ፣ ሱዳንና ጅቡቲ በተለያየ ምክንያት ከውድድሩ ውጪ መሆናቸው የሚታወስ ነው።

ዋልታ ቴሌቪዥን የዛሬውን ጨዋታዎች ከቴሌቪዥን በተጨማሪ በሁሉም የማኅበራዊ ትስስር ገጾች እንደሚያስተላልፍ እየገለጽን እንድትከታተሉ ተጋብዘዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW