የቤኒሻንጉል ክልል የትግራይ ክልልን መልሶ ለማቋቋም የ15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

የካቲት 18፣ 2013 (ዋልታ) – የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የትግራይ ክልልን መልሶ ለማቋቋም የሚውል 15 ሚሊዮን ብር እና የ1 አምቡላንስ ድጋፍ አደርጓል።

እንደ ሀገር ከጁንታው መወገድ በኋላ የትግራይ ክልልን መልሶ-ለማቋቋም በመንግስት እየተሠራ ያለው ሥራ መልካምና የሚደገፍ መሆኑንም የክልሉ መንግስት ይገልጻል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ወደፊትም የትግራይ ክልልን መልሶ-ለማቋቋም የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።