የትራንስፖርት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች ከ57 ሚሊየን ብር በላይ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለመድረግ ቀል ገቡ


ነሀሴ 3/2013 (ዋልታ) –
የትራንስፖርት ሚኒስቴር እና በስሩ ያሉ 10 ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የአንድ ወር የተጣራ ደምዎዛቸውን ድጋፍ አደረጉ፡፡

የሚኒስቴር መስሪያቤታችንና የተጠሪ ተቋማት 17ሺህ 754 አመራር እና ሰራተኞች ናቸው ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ በማበርከት ከሰራዊቱ ጎን መሰላፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡
የሚኒስቴሩ እና የዘጠኝ ተጠሪ ተቋማት አመራርና ሰራተኞች የአንድ ወር የተጣራ ደምዎዛቸውን የለገሱ ሲሆን የሁለት ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች እና አመራሮች የግማሽ ወር ደምዎዛቸውን ነው የለገሱት፡፡
ሰራተኞቹ ሀገራችንን ከውስጥ ባነዳዎችና የውጭ ጣለቃ ገብ ጠላቶች ለመከላከል የሚደረገውን ሀገራዊ ጥሪ በየትኛውም አይነት መስወአዕትነት ለማገልገል ፍቃደኛ መሆናቸውን በመግለጽ ከሰራዊቱ ጎን መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በዚህም በአጠቃላይ 57 ሚሊየን 789 ሺህ 787.50 ብር ቃል መገባቱ ተገልጿል፡፡