የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ በ5 ወራት ብቻ ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ

የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ባለፈው ህዳር ወር ብቻ ከ2.83 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡
ቢሮው ከሐምሌ 1 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም ባሉት አምስት ወራት ከ21.4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ 20 ቢሊዮን 067 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ጠቅሷል።
በዚህም የእቅዱን 93.45 በመቶ ማሳካት መቻሉን ገልጿል።
ቢሮው በህዳር ወር ብቻ ብር 2.77 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 2 ቢሊዮን 838 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን እና ይህ አፈጻጸም በመቶኛ ሲሰላ 102 በመቶ መሆኑን ጠቁሟል፡፡
አፈፃፀሙ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸርም የ1.15 ቢሊዮን ብር ወይም የ6.1 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን ቢሮው ገልጿል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በዘንድሮው በበጀት ዓመት ለመሰብሰብ ከታቀደው አጠቃላይ ገቢ ባለፉት አምስት ወራት ብቻ 47.24 ከመቶው እንደተሰበሰበ ቢሮው ጨምሮ ገልጿል።
ይህ ስኬት የተገኘው የገቢ አሰባሰብ ተቋማዊ ሪፎርሙ በአግባቡ ተግባራዊ በመደረጉ እንዲሁም በየደረጃው ያሉ አመራሮች እና ባለሙያዎች ተቀናጅው በመስራታቸው መሆኑን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡