የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴካፋ ዞን የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን አሸነፈ

ነሀሴ 23/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የሴካፋ ዞን የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን አሸነፈ።
በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ሲካሄድ በቆየው ውድድር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ኬኒያ ፖሊስ ቡሌትን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ ብቸኛውን የማሸነፊያ ግብ ሴናፍ ዋቁማ አስቆጥራለች።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ምስራቅ አፍሪካን በመወከል የሚወዳደር ይሆናል ።
በሙባረክ ፋንታው