ነሐሴ 30/2013 (ዋልታ) ኢትዮጵያዊያን የአገራቸውን ክብርና ጥቅም በዓለም ዐቀፉ መድረክ ለማስጠበቅ በአዲሱ የዲጅታል ዲፕሎማሲ መድረክ እንዲታገሉ ተጠየቀ።
ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ዲጂታል ዲፕሎማሲ አስፈላጊ በመሆኑ በዩኒቨርሲቲዎች የዲጂታል ዲፕሎማሲ ማዕከላትን የማቋቋም ሥራ ተጀምሯል።
የዚሁ አካል የሆነው መርሃ ግብር በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተከውኗል።
በዚህም “የተግባቦት እጥረት የውድቀት መሰረት ነው፤ እኛ በማኅበረሰብ ውስጥ ነን” በሚል መሪ ቃል በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነትት የተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች እና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እየተወያዩ ነው።
በመድረኩ ለአገራቸው ሉኣላዊነት ሲሉ ግንባር ለዘመቱ የሰራዊት ልጆች የሚሆን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እና የአረጋዊያን ቤት እድሳት ሥራ ይከናወናል።
በሜሮን መስፍን