ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በምዕራብ ደንቢያ እየለማ ያለን የስንዴ ማሳ እየጎበኙ ነው

መጋቢት 11/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአማራ ክልል በምዕራብ ደንቢያ እየለማ ያለን የስንዴ ማሳ እየጎበኙ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመራሮች ከፖለቲካና ስብሰባ ጊዜ ቀንሰው ለኢኮኖሚው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በጉብኝቱ እንደተገለጸው ተስፋ ሰጪ የበጋ ስንዴ ልማት እየተካሄደ ሲሆን በአማራ ክልል 2 ሚሊየን ኩንታል የስንዴ ምርት ይጠበቃል።
በጉብኝቱ ላይ የአማራ፣ የኦሮሚያ እና የደቡብ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች መገኘታቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል።