መጋቢት 11/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት በአማራ ክልል በምእራብ ደምቢያ የጎበኙት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ምርታማነት ተስፋ ሰጪ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ግብርና የሀገራችን የኢኮኖሚ መሠረት ሆኖ ቆይቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የስንዴ አቅርቦት በዓለም ዐቀፍ ሁነቶች ጫና እየደረሰበት በመሆኑ፣ በምግብ ራሳችንን ለመቻል ምርታማነታችንን ማፋጠን በእጅጉ ያስፈልገናል ብለዋል።
የግብርና ጉዟችን አድካሚ ቢሆንም ነገር ግን ተጋድሏችን የምርታማነታችንን መጠን በሚሊዮኖች ለማስፋፋት እንደሆነም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት አመልክተዋል፡፡