ፈረንሳይ የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን እድሳት እቀጥላለሁ አለች

ኅዳር 23/2014 (ዋልታ) በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ያለው ጦርነት ከተጠናቀቀ በኋላ ፈረንሳይ የጀመረችውን የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት እድሳት ፕሮጀክት እንደምታስቀጥል አስታወቀች፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ በኢትዮጵያ ከፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማቬሹ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ጦርነት ከተጠናቀቀ በኋላ ፈረንሳይ የጀመረችውን የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እድሳት ፕሮጀክት እንደምታስቀጥል አምባሳደሩ መግለጻቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ላሊበላ ከሽብር ቡድኑ ወረራ ነፃ ስለወጣች የተፈናቀሉ የከተማዋ ዜጎች ከተቋቋሙ በኋላ ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ እንደሚጀምር ያላቸውን እምነትም አምባሳደሩ መግለጻቸውን ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!