ፊፋ ከኳታሩ ዓለም ዋንጫ 6.4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ይጠብቃል

ኅዳር 7/2015 (ዋልታ) የፊታችን እሁድ የሚጀመረው የኳታሩ ዓለም ዋንጫ ለአሸናፊዎች በሚሰጠው ሽልማት መጠን ከዚህ ቀደም ከተዘጋጁት የዓለም ዋንጫዎች ሁሉ የተለየ ያደርገዋል፡፡

በኳታሩ የዓለም ዋንጫ 440 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ሲዘጋጅ፤ የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ለሚያሸንፈው ሀገር 44 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ይበረከትለታል፡፡

የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር ከኳታሩ የዓለም ዋንጫ 6.4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ እንደሚያገኝም እየተናገረ ነው፡፡

ባለፈው የሩሲያው ዓለም ዋንጫ ፊፋ 4.6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ያገኘ ሲሆን ይህ ገቢ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጨምር ይጠበቃል፡፡

የፊፋ ዋንኛው ገቢ ከቴሌቪዥን መብት ሽያጭ የሚገኝ ሲሆን በዚህም 4.6 ቢሊዮን ዶላይ እንደሚገኝ ይጠበቃል፡፡

አልጄዚራ እንደዘገበው ፊፋ ቀሪዎቹን ገቢዎች ከማስታወቂያ፣ ትኬት ሽያጭ እና ብራንዲንግ ነው የሚሰበስበው፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW