ፌዴሬሽኑ የፕሬዝዳንት እና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ምርጫ እጩዎች ዝርዝር ይፋ አደረገ

ሐምሌ 26/2014 (ዋልታ) የምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴ ነሐሴ 21/2014 የሚካሄደው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና ስራ አስፈፃሚ ምርጫ እጩዎችን ይፋ አደረገ።

የምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሐምሌ 22 እና ሐምሌ 25 ባደረገው ስብሰባ ለምርጫው በእጩነት የቀረቡት ተወዳዳሪዎችን ዝርዝር ተመልክቶ ተገቢነታቸውን በማረጋገጥ በዛሬው ዕለት የ3 ፕሬዝዳንት እና 26 የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ተወዳዳሪ እጩዎችን ዝርዝር አሳውቋል።