1ኛው ዙር የሴቶች ፕርሚየር ሊግ ጨዋታ ተጠናቀቀ

የ2013 ዓ.ም አንደኛው ዙር የሴቶች ፕርሚየር ሊግ ጨዋታ ዛሬ ተጠናቀቀ፡፡

የ2013 ዓ.ም አንደኛው ዙር የሴቶች ፕርሚየር ሊግ ፍጻሜ ውድድር መደረጉን ተከትሎ ድሬዳዋ ከተማ ጌዴኦ ዲላን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

በውድድሩ መዝጊያ ላይም የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኤልያስ ሽኩር፣ ምክትል ኮሚሽነር ዱቤ ጅሎ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ስራ አስፈጻሚና የሴቶች የልማትና የውድድር ኮሚቴ ሰብሳቢ ሶፊያ አልማሙን ተገኝተዋል፡፡

እንዲሁም የኮሚሽኑ እና የእግር ኳስ አመራሮችና ባለሙያዎች በሐዋሳ ከተማ ተገኝተው የውድድሩን ሂደት በማየት ስፖርተኞቹን አበራታተዋል።

የሴቶች ፕርሚየር ሊግን የመጀመሪያ ዙር ውድድርን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ27 ነጥቦች አንደኛ ሲሆን፣ መከላከያ እና ሀዋሳ ተከታዩን ስፍራ ይዘው አጠናቀዋል፡፡

ሁለተኛው ዙር የሴቶች ፕርሚየር ሊግ ውድድር በአዳማ ከተማ የካቲት ስድስት የሚጀምር ይሆናል፡፡

(ሄኖክ አስራት)