2ኛው የምርጥ ቡና ቅምሻ ውድድር ይፋ ሆነ

ሁለተኛውን ቡና ቅምሻ ‘የካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ’ ውድድር የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን እንዲሁም በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ድጋፍ ዛሬ ይፋ አደረጉ፡፡

የውድድር መጀመር በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበሌ፣ በኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማኅበር የሥራ አመራር ቦርድ ፕሬዝዳንት አቶ ደሳለኝ ጀና እና በውድድሩ አስተባባሪ ወ/ት ቅድስት ሙሉጌታ ዛሬ ይፋ ሆኗል፡፡

እ.ኤ.አ በ1999 በብራዚል የተጀመረው “ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ” ከፍተኛ ጥንቃቄ የተሞላበት ዓመታዊ የቡና ውድድር ሲሆን ግልፅና አስተማማኝ ውድድርን በማካሄድ በዓለም የቡና ገበያ ከፍተኛ ዋጋ ያስገኛል፡፡

የመጀመሪያው ኢትዮጵያ ቡና ቅምሻ ውድድር በ2012 የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን፣ እና በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት በሚደገፈው (Future Ethiopia Value Chain Activity) በመተባበር በጋራ የተካሄደ ሲሆን በውድድሩ በተካሄደ ጨረታ አንድ ኪሎ ግራም ቡና በ407 የአሜሪካን ዶላር ተሽጧል፡፡

(በሶሬቻ ቀበኔቻ)