2ኛ ዙር የፕሪምየር ሊግ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ተከፈተ

የካቲት 24/2014 (ዋልታ) ሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት በዛሬው ዕለት መከፈቱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪምየር ሊግ የ2014 ዓ.ም የ1ኛ ዙር ውድድር መርሃ ግብር የካቲት 23/2014 ዓ.ም ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡

የፕሪምየር ሊጉ የመጀመሪያ ዙር የውድድር መርሃ ግብር መጠናቀቅ ተከትሎ የሁለተኛው ዙር ከመጀመሩ አስቀድሞ የተጫዋቾች ዝውውር ዛሬ የካቲት 24/2014 ዓ.ም ተከፍቷል፡፡

የዝውውር መስኮቱ እስከ መጋቢት 24/2014 ዓ.ም ድረስ ለአንድ ወር የሚካሄድ መሆኑን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW