የትራንስፖርት ቢሮ ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የብስክሌትና እግረኞች ቀን እሁድ ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም በተለያዩ መርሃግብሮች እንደሚያካሂድ ተገለጸ፡፡
በየወሩ በ4ኛው ሳምንት የሚከበረው የብስክሌትና እግረኞች ቀን በከተማዋ የሞተር አልባ ትራንስፖርት አገልግሎትን ማስተዋወቅ እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም ማህበረሰቡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ጤናውን እንዲጠብቅ ከማስቻሉ ባለፈ ብስክሌት አማራጭ የትራንስፖርት ስልት እንዲሆን ግንዛቤ ለማስጨበጥ እገዛ እንደሚያደርግ ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡