4ኛው የብስክሌተኞችና እግረኞች ቀን በመጪው እሁድ ይካሄዳል

                                                          4ኛው የብስክሌተኞችና እግረኞች ቀን

የትራንስፖርት ቢሮ ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የብስክሌትና እግረኞች ቀን እሁድ ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም በተለያዩ መርሃግብሮች እንደሚያካሂድ ተገለጸ፡፡

በየወሩ በ4ኛው ሳምንት የሚከበረው የብስክሌትና እግረኞች ቀን በከተማዋ የሞተር አልባ ትራንስፖርት አገልግሎትን ማስተዋወቅ እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ማህበረሰቡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ጤናውን እንዲጠብቅ ከማስቻሉ ባለፈ ብስክሌት አማራጭ የትራንስፖርት ስልት እንዲሆን ግንዛቤ ለማስጨበጥ እገዛ እንደሚያደርግ ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡