ነሐሴ 16፣ 2008 (ዋኢማ)- በ2008 ዓ.ም አጠቃላይ እንቅስቃሴዎች 27 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታውቋል።
ከባንኩ አጠቃላይ ገቢ ውስጥም 13 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብሩ ያልተጣራ ትርፍ መሆኑ ተገልጿል።
በበጀት ዓመቱ ከወጪ ንግድ፣ ከውጭ ሀገራት ከሚላክ ገንዘብ እና ከሌሎች የተለያዩ ምንጮች 4 ነጥብ 7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር መሰብሰብ እንደቻለ ባንኩ አስረድቷል፡፡
ሀገሪቱ ለምታከናውናቸው የልማት ስራዎች ግብአቶችን ከውጭ ለማስገባት፣ ለነዳጅና ሀገሪቱ ለምታከናውናቸው የተለያዩ ግዥዎች 6 ነጥብ 8 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ክፍያም ፈጽሜያለው ብሏል።
አሁን ላይ የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 384 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉንም ይፋ አደርጓል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮንስትራክሽን እና ቢዝነስ ባንክን በበጀት አመቱ መጠቅለሉ ይታወሳል።(ኤፍ.ቢ.ሲ)