የኢትዮጵያ ሰሊጥ ከዓለም ምርጡ መሆኑ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ሰሊጥ ከዓለም ምርጡ መሆኑን ምርት መሆኑ ተገለጸ

በኢትዮጵያ በተለይ በትግራይ የሑመራ ሰሊጥ በመካከለኛው ምስራቅና በሌሎች አገሮች በእጅጉ ተፈላጊ መሆኑ ተገልጿል ፡፡ 

በሀገሪቱ እህሉን በስፋት ለማቀነባበር የሀብት እጥረት በመኖሩ ምክንያት አብዛኛው የኢትዮጵያ የሰሊጥ ምርት በእስራኤልና ቱርክ አገሮች ተቀነባብሮ ለዓለም ገበያ ይቀርባል ነው የተባለው ፡፡

በባለፉት ሁለት ዓመታት የዓለም የሰሊጥ እህል በ20 በመቶ ፍላጎቱ መጨመሩን ነው የተጠቆመው፡፡

አብዛኛው የሰሊጥ ምርት ዘይት፣ ዳቦ፣ ኬክና ሌሎች መሰል ጣፋጭ ምግቦችን ለማዘጋጀት ጥቅም ላይ ይውላል

ሀገራችን ወደ ውጭ ከምትልካቸው የግብርና ውጤቶች ከቡና ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ነው የተመለከተው -(ሳቮይር ድረ-ገጽ ) ፡፡