በዓለም አቀፉ ደረጃ ግዙፍ የሆነው የፒዛ ሃት ሬስቱራንት ድርጅት በኢትዮጵያ ሥራ ለመጀመር መዘጋጀቱን አስታወቀ።
ዓለም አቀፉ የፒዛ ሃት በዘንድሮ ዓመት የፈረንጆች ዓመት ሦስት ደረጃቸውን የጠበቁ ሬስቱራንቶችን ለአገልግሎት ለማብቃት ዕቅድ ይዟል ተብሏል ።
የፒዛ ሃት ድርጅት ጋር በአጋርነት የሚሠራው በላይአብ ከተባለው የምግብ ተቋም ሲሆን በአጠቃላይ ለሬስቱራንቶቹ ግንባታ 5 ነጥብ5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ እንደሚሆን ተመልክቷል ።
የበላይ አብ ምግብና የያም ብራንድ ተወካይ አቶ አስቻለው እንደገለጹት ድርጅቱ በመጪው ህዳር የሬስቱራንቶችን ግንባታ በማጠናቀቅ በአዲስ አበባ ከተማ አገልገሎት መሥጠት ይጀምራል ።
ፒዛ ሃት በኢትዮጵያ የሚከፍታቸው ሬስቱራንቶች ከሳሃ በታች ባሉ አፍሪካ አገራት የመጀመሪያዎቹ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን ድርጅቱ በኢትዮጵያ ብራንዱን ለማስፋፋት ያነሳሳው ርካሽ የሰው ሃይል ፣ ቅናሽ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልገሎት መኖሩናበዘርፉ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪዎች አለመኖራቸው እንደሆነ ተመልክቷል ።
ፒዛ ሃት በኢትዮጵያ ሬስቱራንቶቹን ካስፋፋ በኋላ በአጠቃላይ በዘንድሮ የበጀት ዓመት በአፍሪካ ከ70 በላይ ሬስቱራንቶችን ለመክፈት ማቀዱን የድርጅቱ የአፍሪካ አህጉር ዋና ሥራ አስኪያጅ እዋን ዴቭን ፖርት ተናግረዋል ።
በአፍሪካ እስካሁን ድረስ ግማሽ የሚሆነው የፒዛ ንግድ በደቡበ አፍሪካ የሚገኝ ሲሆን ድርጅቱ እኤአ በ2015 በደቡበ አፍሪካ ራስቱራንቶችን መክፈት መጀመሩ ተገልጿል ።
ፒዛ ሃት በጋና ሬስቱራንቶችን ለማስፋፋትም ዕቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዘንድሮ የፈረንጆች ዓመት የ7ነጥብ 5 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ በአፍሪካ ከአይቮሪ ኮሰት ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እንደምታስመዘግብ መተንበዩ ይታወሳል ።( ምንጭ : ብሉምበርግ )