በተያዘው የ2018 ዓመት የግብፅ የኢኮኖሚ አምስት በመቶ እንደሚያድግ ዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤም ኤፍ) አስታውቋል፡፡
ግብጽ የተተነበየውን እድገት ለማስመዝገብ ቢያንስ ለ700 ሺህ ዜጎቿ የሥራ እድል መፍጠር እንዳለባትም ተቋሙ ገልጿል፡፡ የግል የኢንቨስትመንት ዘርፉን ማስፋፋት ትኩረት ሊሠጠው ይገባል ተብሏል፡፡
ሁሉን አቀፍ ዕድገት ማጎልበት በሚል ሓሳብ ዙሪያ የሚያጠነጥን ስብሰባ በሞሮኮዋ ማራካሽ ከተማ ተካሂዷል፡፡ ይህ ስብስባ የአረቡን ዓለም ኢኮኖሚ ለማሳደግ እና የሥራ እድልን ለሁሉም ማዳረስ በሚቻልበት ሁኔታ መክሯል፡፡
በዓለም ዓቀፍ ልማት ፕሮጀክት የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም የሚያመጣውን መልካም ውጤት በግብጽ ዘንድ ተቀባይነትን አግኝቶ እንዲተገበር በመደረጉ ሀገሪቷ በዚህ ዓመት 5 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት ታስመዘግባለች ተብሎ እንደሚጠበቅ በዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም የመካለለኛው ምስራቅና መካከለኛው እሰያ ፈንድ ዳይሬክተር ጂሃድ አዞር ገልፀዋል፡፡
ይህ ደግሞ ሀገሪቷ የኢኮኖሚ እድገቷን ለማፋጠን ትልቁን ድርሻ ይወስዳል ብለዋል፡፡ ዳይሬክተሩ ይህን ያሉት በማራካሹ ስብሰባ ላይ ተግኝተው ነው፡፡
የግብፅ መንግስት ያደረገው ማሻሻያ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኝ እና ተጨማሪ የኢንቨስትመንት አውታሮችን በማስፋት የብድር አገልግሎትን ማስገኘት ረገድ ውጤት እያሰገኘ ይገኛልም ብለዋል፡፡
እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ግብፅ የሚያግጥሟትን ዋነኛ የኢኮኖሚ ፈተናዎች ለመቋቋም የሀገሪቱ መንግስት የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎችን መውሰድ፣ በየአመቱ 700 ሺህ ለሚሆኑ ስራ አጥ ዜጎች ስራ መፍጠር ይኖርበታል፡፡
ይህ ከተደረገ ሀገሪቱ የሚያጋጥማትን በጀት ጉድለት መቀነስም ያስችላል ማለታቸውን ኢጂፕት ኦን ላይን የተባለ ድረገፅ ዘግቧል፡፡
ማሻሻያው ሀገሪቷ በዓረቡ ዓለም ያላትን ቁልፍ የኢኮኖሚ ሚና በመመለስ፣ ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶችን በማስፋፋት እና ኢንቨስትመንትን በማበረታታት ረገድ ጉልህ ሚና ይጫወታልም ብለዋል፡፡
የግሉ ዘርፍ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ልማት ውስጥ የበለጠ እድል ሊሰጠው እንደሚገባ በዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም የመካከለኛው ምስራቅና መካከለኛው ኤስያ ዳይሬክተር ጂሃድ አዞር አመልክተዋል፡፡