የባሌ-ሮቤ አየር ማረፊያ አገልግሎት መሥጠት ጀመረ

የባሌ-ሮቤ አየር ማረፊያ አገልግሎት መሥጠት መጀመሩ ተገለጸ ።

የባሌ-ሮቤ አየር ማረፊያው በትናንትናው እለት ነው በይፋ ተመርቆ ለደንበኞች  አገልግሎት የመሥጠት ሥራ የጀመረው፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ባሌ የበረራ አገልገሎት የሚሠጠው  በሳምንት ሶስት ቀን ረቡዕ፤ አርብ እና እሁድ  እንደሆነ ታውቋል፡፡

ከአዲስ አበባ ባሌ-ሮቤ ለመድረስም 40 ደቂቃ እንደሚወስድ ተገልጿል፡፡

በ2007 ዓ.ም ግንባታው የተጀመረው የአውሮፕላን ማረፊያው በ500 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባ ሲሆን ወጪውን የፌደራል መንግስት እንደመደበ ታውቋል፡፡

አየር ማረፊያው ሶስት ነጥብ አራት ኪሎ ሜትር ርዝመት እና ስልሳ ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን ቦዪንግ 737 ጨምሮ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ አውሮፕላኖችን የማስተናገድ አቅም እንዳለው ተጠቁሟል፡፡