የጥቅምት ወር የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

የጥቅምት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ለዋልታ በላከው መግለጫ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር ሌሎች የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ብሏል።

የአውሮፕላን ነዳጅ በመስከረም ወር በሊትር ሲሸጥበት ከነበረው 24 ብር ከ61 ሳንቲም የ1 ብር ከ11 ሳንቲም ጭማሪ አሳይቷል።

በዚህም መሰረት አንድ ሊትር የአውሮፕላን ነዳጅ በ25 ብር ከ72 ሳንቲም እንደሚሸጥ የሚኒስቴሩ መግለጫ ያመላክታል።