ኢትዮጵያ 19 በመቶ ባለድርሻ የሆነችበት የሶማሊ ላንድ በርበራ ወደብ ግንባታ ተጀመረ

ኢትዮጵያ 19 በመቶ ባለድርሻ የሆነችበት የሶማሊ ላንድ በርበራ ወደብ ግንባታ ተጀመረ፡፡ 

የግንባታ ማስጀመር ስነ ሥርዓቱ ጥቅምት 1፣ 2011 አመተ ምህረት ሲካሄድ የኢትዮጵያ መንግስት፣ የሶማሊ ላንድ አስተዳድርና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ተወካዮች ተካፍለዋል፡፡

ዲፒ ወርልድ የተባለው የኤምሬትስ ኩባንያ በ420 ሚሊዮን ዶላር የበርበራ ወደብን ግንባታ ለማካሄድ ውል ገብቶ ስራውን ጀምሯል፡፡

በስምምነቱ መሰረት በወደቡ ግንባታ   የተባበሩት አረብ ኤምሬቱ ዲፒ ወርልድ 51 በመቶ፣ የሶማሊ ላንድ አስተዳደር 30 በመቶ እና የኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ 19 በመቶ ድርሻ ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡

ከግንባታ በኋላ ስምምነቱ ለ30 ዓመት የሚቆይ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

የሶማሊ ላንድ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ በሥነ -ሥርዓቱ ላይ እንደተናገሩት፥ የበርበራ ወደብ ግንባታ እውን መሆን የሶማሊ ላንድ ኢኮኖሚን ከማነቃቃት ባሻገር ለቀጠናው የንግድና ኢኮኖሚ  ትስስር ፋይዳው የጎላ ነው፡፡ (ምንጭ:የሶማሌ ላንድ ሰን)