የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ኢግዝብሺን ማዕከል የንግድ ባዛር ተከፈተ

13ኛውን የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ኢግዚብሽን ማዕከል የንግድ ባዛር ተመርቆ ተከፈተ፡፡

በባዛሩ ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ሞዴል ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ዋልታ ያነጋገራቸው የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን አስመልክተው እንደዚህ መሰል እግዝብሺኖች መከፈታቸው የገበያ ትስስርን ከማጠናከር ባለፈ የልምድ ልውውጥን ለማድረግ ይጠቅማል ብለዋል፡፡

በመክፈቻ ሥነሥርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፌደሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፌጉባኤ አቶ መሐመድ ረሽድን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡