የኢትዮጵያ ልዑክ ከዓለም የአልባሳት ዘርፍ ታዋቂ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አደረገ

የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ልዑክ በዓለም ደረጃ በአልባሳት ዘርፍ  ታዋቂ ምልክት ካላቸው የተለያዩ  ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በሆንግ-ኮንግ ውይይት ማድረጉ  ተገለጸ ።        

በውይይቱ ኩባንያዎቹ የኢትዮጵያን ምርት እንዲገዙና ለእነሱ ምርታቸውን በማቅረብ ላይ የሚገኙ የጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ፋብሪካዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው መዋለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።

የፒ ቪ ኤች ምክትል ፕሬዚዳንት በሆንግ-ኮንግ ተገኝተው በሓዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ያላቸውን መልካም ተሞክሮ ለብራንድ አመራሮቹ ገልጸዋል።

ተሳታፊዎቹም ዘርፉን ለማሳደግ በትብብር እየተሠራ ያለውን ሂደት ያደነቁ ሲሆን፥ በተለይ ዘላቂ እንዲሆን በዕውቀት ላይ ተመሥርቶ በተሄደበት ርቀት የጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት የመጨረሻ ማረፊያ የሆነችውን አፍሪካን እንዲሁም ኢትዮጵያን ይበልጥ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። 

በውይይቱ  ወቅትም የዓለም አቀፍ ተቋማት ከኢትዮጵያ ጋር  በጋራ ለመሥራት ቁርጠኛ አቋም ያላቸው መሆኑም  ተገልጿል ።