አየር መንገዱ 10ኛውን ኤር ባስ ኤ 350 አውሮፕላን ተረከበ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 10ኛውን ኤር ባስ ኤ 350 አውሮፕላን ተረክቧል።

የርክክብ ስነ ስርዓቱ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም፣ አምባሳደሮችና የኤር ባስ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም እንደገለጹት አየር መንገዱ የመጀመሪያውን ኤር ባስ ኤ 350 አውሮፕላን በፈረንጆቹ 2016 ዓ.ም ተረክቧል።

ሁለት ዓመት ተኩል ባልሞላ ጊዜ ውስጥም 10 ተመሳሳይ አውሮፕላኖችን መረከብ ችሏል ነው ያሉት።

ኤር ባስ ኤ 350 አውሮፕላን ከዓለማችን ዘመናዊ አውሮፕላኖች አንዱ ሲሆን፥ የዛሬው አውሮፕላን አየር መንገዱ የነበሩትን መሰል አውሮፕላኖች ቁጥር ከፍ ያደርገዋል።

343 የአየር መንገዱን ደንበኞች በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችለው ይህ አውሮፕላን የአየር መንገዱን ተደራሽነት በማስፋት የደንበኞችን እርካታም ከፍ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ ባለፈም አሁን ላይ አየር መንገዱ በተለያዩ የዓለም አካባቢዎች ለጀመረው የበረራ መዳረሻ ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያደርግም ታምኖበታል።

(ኤፍ.ቢ.ሲ)