የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞስኮ በረራ ጀመረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ 27 ዓመት ወደ ሞስኮ የሚያደርገውን በረራ በይፈ ጀምሯል፡፡

በረራው የሚደረገዉ  በሳምንት 3 ቀን ከአዲስ አበባ ሞስኮ የሚደረግ ይሆናል።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም፥ አየር መንገዱ በሳምንት 3 ቀን ወደ ሞስኮ የሚጀምረው በረራ ወደ አውሮፓ የሚያደርገውን በረራ ወደ 54 ያሳድገዋል ብለዋል።

ይህም ለንግድና ባህል ልውውጥ እንዲሁም ለቱሪዝምና ኢንቨስትመንት መስፋፋት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል ነው ያሉት።

በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የሃይማኖት መሪዎችና የተለያዩ እንግዶች መታደማቸዉ ነዉ የተለጸዉ፡፡

አየር መንገዱ ከ1983 ዓም ጀምሮ ወደ ሞስኮ የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡ ይታወሳል፡፡